በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጋዛ  በሚገኝ ትምሕርት ቤት ላይ ጥቃት አድርሳ ቢያንስ 30 ሰዎች መግደሏን የጋዛ የጤና ሚንስቴር ገለጸ


እ.ኤ.አ. ጁላይ 27፣ 2024 በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በዴር አል ባላህ የእስራኤል አድማ ተከትሎ ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮችን የሚጠለሉ ትምህርት ቤቶችን ቃኙ።
እ.ኤ.አ. ጁላይ 27፣ 2024 በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ውስጥ በዴር አል ባላህ የእስራኤል አድማ ተከትሎ ፍልስጤማውያን ተፈናቃዮችን የሚጠለሉ ትምህርት ቤቶችን ቃኙ።

እስራኤል ማዕከላዊ ጋዛ ዴር አል ባላ በተባለ አካባቢ ጥቃት አድርሳ ቢያንስ 30 ሰዎች መግደሏን የፍልስጥኤማዊያን የጤና ባለሥልጣናት ተናገሩ።

የእስራኤል የጦር ኃይል በበኩሉ የደበደብነው የሃማስን የእዝ ማዕከል ነው ብሏል። የጋዛ የጤና ሚንስቴር እና ሐማስ የሚያስተዳድረው መንግሥት የዜና ማሰራጫዎች ተፈናቃይ ቤተሰቦች በብዛት የተጠለሉበት በሆነው አካባቢ በደረሰው ጥቃት ከተገደሉት በተጨማሪ ከአንድ መቶ የሚበልጡ ሰዎች እንደቆሰሉ አመልክተዋል።

የእስራኤል የጦር ኃይል ባወጣው መግለጫ በበኩሉ " ማዕከላዊ ጋዛ በሚገኘው ኻዲጃ ትምሕርት ቤት ያለ የሀማስ የተዋጊ የእዝ እና ቁጥጥር ማዕከል አጥቅተናል" ብሏል።

ዛሬ ቀደም ብሎ የፍልስጥኤም አስተዳደር የዜና ማሰራጫዎች ባወጡት ዘገባ እስራኤል ከንጋት አንስታ ደቡባዊ ካን ዩኒስ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል።

የእስራኤል የጦር ኃይል ጥቃቶቹን አጠናክሮ ለማካሄድ በሚል ፍልስጥኤማዊያን በጊዜያዊነት ከደቡባዊ ካን ዩኒስ ወጥተው አል ማዋሲ ወደሚገኝ አካባቢ እንዲሄዱ አሳስቦ እንደነበር አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG