በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'ከባድ ዝናም' የፓሪሱን ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንዳያደበዝዝ አስግቷል

 የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትን ከአይፍል ታወር ፊት ለፊት የሚጠባበቁ ጥንዶች፡፡ ፓሪስ፣ ፈረንሳይ ፣ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Alessandra Tarantino)
የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓትን ከአይፍል ታወር ፊት ለፊት የሚጠባበቁ ጥንዶች፡፡ ፓሪስ፣ ፈረንሳይ ፣ ሐምሌ 19 ቀን 2016 ዓ.ም. (AP Photo/Alessandra Tarantino)

የዘንድሮው የፓሪስ ኦሊምፒክ መጀመሪያ በዝናም የታጀበ ይሆናል ተብሏል። በፈረንሳዩ የሜቶሮሎጂካል አገልግሎት - ሜቲዮ-ፍራንስ ትንበያ መሰረት የመክፈቻው ሥነ ሥርዓቱ ምሽቱን የፓሪሱን የሴን ወንዝ ተከትሎ ካለው ሥፍራ በሚካድበት ሰዓት ዝናሙም ዘለግ ብሎ መውረዱን እንደሚቀጥል ነው የተተነበየው።

ይሁን እንጂ ከሶስት ሰአታት በላይ የሚዘልቀው የመክፈቻ ትርኢት በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከግማሽ ሰአት በፊት እንዲጀምር ተደርጓል።

ከቀትር በኋላውን ደመና ከባብዶት የዋለው የፓሪስ ሰማይ መጠነኛ ካፊያ አልተለየውም ነበር። በበጎ ጎን የታየው ሌላ ገጽታው የአካባቢው የሙቀት መጠን በአንጻሩ ምሽቱን ሞቅ እንዳለ እንደሚቀጥል መገመቱ ነው።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG