የካናዳ የሴቶች እግር ኳስ አሰልጣኝ ቤቭ ፕሪስትማን በሰው አልባ አውሮፕላን ከተፈጸመ የስለላ ድርጊት ጋር በተያያዘ ቅሌት ከሥራቸው ታግደው ለኦሎምፒክ ውድድሩ ወደ ፓሪስ ከሚሄደው ቡድናቸውም እንዲወገዱ ተደርገዋል።
“ከአጠቃላይ የሥርአት መጓደል ጋር የተዛመደ የሥነ ምግባር ጉድለት” ያሉት መኖር ያለመኖሩን ለማረጋገጥ የሚያስችል ምርመራ እያካሄዱ መሆናቸውን የገለጹት የካናዳ እግር ኳስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና ዋና ፀሃፊ ኬቨን ብሉ ሲያስረዱ “በካናዳ የሴቶች ቡድን ውስጥ ያሉ ተጫዋቾች በፓሪስ ኦሎምፒክ በምንም አይነት ሥነ ምግባር የጎደለው ድርጊት አልተሳተፉም” ብለዋል።
ብሉ አክለውም ፕሪስትማን ከቡድኑ ጋር ሊኖራቸው የሚችለው ግንኙነትም "ሙሉ በሙሉ ከግምገማው በሚገኝ ውጤት የሚወሰን ይሆናል" ብለዋል።
መድረክ / ፎረም