የሳምንታት መላምትን እንዲሁም ከዲሞክራቲክ ፓርቲያቸውም ጭምር ከፍተኛ ግፊት ማየሉን ተከትሎ፣ ፕሬዝደንት ባይደን ትላንት እሁድ ከፕሬዝደንታዊ ምርጫው ራሳቸውን አግልለው፣ ምክትል ፕሬዝደንት ካመላ ሄሪስ ለቦታው እንዲወዳደሩ ድጋፋቸውን መግለጻቸው በመላ ሃገሪቱ የክውታ ሞገድን አንዝሯል።
የቪኦኤው ሪቻርድ ግሪን የባይደን ከውድድሩ ራሳቸውን ማግለል የ2024ቱን ምርጫ በምን መልክ እንደሚቀይረው ተመልክቷል።