ዋሽንግተን —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ለ2024 ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ከቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋራ ከገቡበት የድጋሚ ምርጫ ፉክክር ራሳቸውን አገለሉ። ምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስን በዕጩነት አቀረቡ።
ለኮቪድ-19 ሕመም መጋለጣቸውን ተከትሎ፣ ራሳቸውን ከሌሎች ለይተው በዴላዌር በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው በማገገም ላይ የሚገኙት ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ምክትል ፕሬዝደንት ካማላ ሃሪስን የዴሞክራት ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ ዕጩ አድገው አቅርበዋል።
ካማላ በ248 ዓመት የዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት እና የደቡብ እስያ አሜሪካዊ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ይኾናሉ።
ባይደን በሰኔ ወር መጨረሻ ላይ ከዶናልድ ትራምፕ ጋራ ያደረጉትን ፕሬዝደንታዊ ክርክር ተከትሎ፣ በድጋሚ ለመመረጥ የሚያደርጉት የምርጫ ዘመቻቸው እንዲያቋርጡ እና ከዕጩነቱ እንዲወጡ የሚጠይቁ ዴሞክራቶች ቁጥር እየጨመረ ነበር።
መድረክ / ፎረም