በመንግስት የተከለከለን ጸረ- ሙስና ሰልፍ የፊታችን ማክሰኞ ለማከናወን በያዙት ዕቅድ እንደሚገፉ እየተናገሩ የሚገኙ ዮጋንዳዊያን ተቃዋሚ ሰልፈኞች " በእሳት እየተጫወቱ ነው " ሲሉ የሀገሪቱ ፕሬዚደንት አስጠነቀቁ ።
"አንዳንድ አካላት ህገወጥ ሰልፍ ለማድረግ ፣ ነውጥ ለመፍጠር አቅደዋል!" ፣ ብለዋል ፕሬዚደንት ዮሪ ሙሴቬኒ ቅዳሜ ምሽት በተላለፈ የቴሌቭዥን መልዕክታቸው ። ሙሴቬኔ ምስራቅ አፍሪካዊቷን ሀገር ከ1986 የአውሮፓዊያኑ ዘመን ጀምሮ በጠንካራ ክንድ መርተዋል ። እሳቸው ካለ ተጨማሪ ማብራሪያ ፣ "ለውጭ ሀገራት ፍላጎት የሚሰሩ አካላት " በተቃውሞ ሰልፈኞች መካከል እንደሚገኙ ተናግረዋል ።
ቅዳሜ ማለዳ ላይ የዩጋንዳ ፖሊስ ለአስተባባሪዎች በመዲናዋ ካምፓላ ሊደረግ ለታቀደው ሰልፍ ፍቃድ እንደማይሰጥ አስታውቋል ። ባለስልጣናት አንዳንድ አካላት ሰልፉን በሀገሪቱ ብጥብጥ በመቀስቀስ ለራሳው ጥቅም ለማዋል ስለማቀዳቸው የቀደመ መረጃ ደርሶናል ብለዋል ።
የህዝብ ብጥብጥ መንስኤ የማይሆኑ እና የሕጋዊ ዜጎችን ህይወት የማይረብሹ ሰልፎች የመፍቀድ ብቸኛ ስልጣን ያለው ፖሊስ ብቻ መሆኑን ፣ የሀገሪቱ ፖሊስ ስምሪት ኃላፊ ፍራንክ ምውሲጋዋ ለኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል ።
የሰልፉ አስተባባሪዎች ግን በዕቅዳቸው እንደሚቀጥሉ ለኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል ።
"በሰልፉ ለመቀጠል የፖሊስ ፍቃድ አያስፈልገንም " ያሉት ከሰልፍ ዋነኛ መሪዎች መካከል አንዱ የሆኑት ሉዊዝ አሎይኪን ኦፖሊሲ ፣ " ህገ መንግስታዊ መብታችን ነው " ብለው በትናትናው ዕለት ።
ተቃዋሚ ሰልፈኞች ፣ ሙስናን ችላ ብሏል ሲሉ በሚከሱት የሀገሪቱ ፓርላማ በኩል ለማለፍ ተስፋ ሰንቀዋል ። ትራንስፓሬንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም በዩጋንዳ ያለው የሙስና ግንዛቤ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጠዋል ። መጠነኛ ሙስና ያለባቸው ሀገራት ከፍተኛውን ደረጃ በያዙበት 180 ሀገራት በተጠቀሱበት ሰንጠረዥ ላይ ዩጋንዳ በ141ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ።
የፀረ-ሙስና ተቃዋሚዎች ጎረቤት ኬንያን ከአንድ ወር በላይ ያናወጠውን አልፎ አልፊ ሞት ያስከተሉ ሰልፎችን ሲከታተሉ ቆይተዋል።
መንግስታዊ ድጋፍ በሚፈረግለት የኬንያ ብሔራዊ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ቆጠራ መሰረት ሰልፉ ጥር 18 ላይ ከጀመረ ወዲህ 50 ሰዎች ሲገደሉ ፣ 413 ተጎድተዋል።
መድረክ / ፎረም