በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ ወደ ምርጫ ዘመቻው ተመልሰዋል


ዶናልድ ትረምፕና ቤተሰቦቻቸው በሪፐብሊካን ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ (ፎቶ ኤፒ ሐምሌ 18፣ 2014)
ዶናልድ ትረምፕና ቤተሰቦቻቸው በሪፐብሊካን ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ ላይ (ፎቶ ኤፒ ሐምሌ 18፣ 2014)

የሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዝደንታዊ እጩ ዶናልድ ትረምፕ፣ ከጎናቸው ሆነው ለምክትል ፕሬዝደንትነት ከሚፎካከሩት ጄ ዲ ቫንስ ጋራ በመሆን ዛሬ የጋለ ፕሬዝደንታዊ የምርጫ ፉክክር እንደሚደረግባት በሚጠበቀው ሚቺጋን ክፍለ ግዛት የምርጫ ዘመቻ ያደርጋሉ።

የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸውና በይፋ በፓርቲው ከታጩ ወዲህ እንዲሁም ለምክትል ፕሬዝደንትነት ከታጩት የኦሃዮው እንደራሴ ጄ ዲ ቫንስ ጋራ የሚያደርጉት የመጀመሪያው የምርጫ ዘመቻ ነው።

የሚቺጋን ግዛት ወደ የትኛውም ፓርቲ ሊያዘነብሉ እና የምርጫውን ውጤት ሊወስኑ ከሚችሉት ግዛቶች አንዷ ስትሆን፣ ትረምፕ ጄ ዲ ቫንስን ከጎናቸው አድርገው ግራንድ ራፒድስ ከተባለችውና ለረጅም ጊዜ ጠንካራ የሪፐብሊካን ደጋፊ የነበረች፣ በቅርብ ጊዜ ምርጫዎች ግን ዲሞክራቶችን ወደመምረጥ እየሄደች ባለችው ከተማ ንግግር ያደርጋሉ።

በሚቺጋን በ2016 በተካሄደው ምርጫ ትረምፕ በ10 ሺሕ ድምጽ ሲያሸንፉ፣ በ2020 በተደረገው ምርጫ ደግሞ ጆ ባይደን በ154 ሺሕ ድምጽ አሸንፈዋል።

የጄ ዲ ቫንስ በምክትል ፕሬዝደንት እጩነት መመረጣቸው በሚቺጋን፣ ፔንስልቬኒያ፣ ውስካንሰን እና ኦሃዮ፣ ትረምፕ በ2016 ያገኙትን ድል እንዲደግሙ ድጋፍ ለማግኘት እንዲያስችላቸው ነው ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG