በሚልዋኪ ከተማ ውስጥ እየተካሔደ ለሚገኘው የሪፐብሊካን ፓርቲ ብሔራዊ ጉባኤ በሚያደርገው ጥበቃ ብቃት እንደሚተማመን የፕሬዚዳንታዊ ደኅንነት አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ትላንት የተከፈተው የፓርቲው ብሔራዊ ጉባኤ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ላይ ከተደረገው የግድያ ሙከራ በኋላ የሚካሔድ መኾኑ፣ የቀድሞው ፕሬዝደንት የደኅንነት ጥበቃ ብቃት ትኩረት እንዲሰጠው አድርጓል፡፡
የአሜሪካ ድምፁ አራሽ አራባሳዲ ያጠናቀረው ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡