በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃማስ "የተኩስ አቁም ድርድሩ አልተቋረጠም፣ አዛዣችን ከእስራኤል ጥቃት ተርፈዋል"አለ


An Israeli soldier moves on the top of a tank near the Israeli-Gaza border, as seen from southern Israel, July 14, 2024.
An Israeli soldier moves on the top of a tank near the Israeli-Gaza border, as seen from southern Israel, July 14, 2024.

ጋዛ ላይ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ የተያዘው ድርድር እንዳልተቋረጠ ሃማስ መናገሩ ተዘገበ።

ትላንት እስራኤል የሃማሱን የጦር አዛዥ መሐመድ ዲየፍን ዒላማ ያደረገ ከፍተኛ የአየር ጥቃት ያካሄደች ሲሆን የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት ህጻናትን ጨምሮ ቢያንስ ዘጠና ሰዎች መገደላቸውን አመልክተዋል። ሃማስ አዛዡ ደህና ናቸው ብሏል።

ትላንት ማታ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መገደል አለመገደሉን መቶ በመቶ እርግጠኛ ሆኖ መናገር አይቻልም ያሉ ሲሆን ስለሁኔታው አሁንም አልታወቀም።

ሆኖም የሃማስ ተጠሪዎች ለጋዛ ጦርነት ምክንያት የሆነው እ.አ.አ በጥቅምት 7 እስራኤል ላይ የተፈጸመው ጥቃት ዋና ዕቅድ አውጪያቸውን ደህንነት በሚመለከት የሰጡትን መግለጫ የሚያጠናክር በማስረጃ አላስደገፉም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG