በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናይሮቢ የቆሻሻ መጣያ ተጨማሪ ተቆራርጠው የተጣሉ የሴቶች አካላት ተገኙ


የኬኒያ ፖሊሶች በናይሮቢ የቆሻሻ ገንዳ ተቆራርጠው በከረጢቶች ተሞልተው የተጣሉ ተጨማሪ የሴት የሰውነት ክፍሎችን ማግኘታቸውን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሰብስበው ሲመለከቱ።
የኬኒያ ፖሊሶች በናይሮቢ የቆሻሻ ገንዳ ተቆራርጠው በከረጢቶች ተሞልተው የተጣሉ ተጨማሪ የሴት የሰውነት ክፍሎችን ማግኘታቸውን ተከትሎ የአካባቢው ነዋሪዎች ተሰብስበው ሲመለከቱ።

የኬኒያ ፖሊሶች በናይሮቢ የቆሻሻ ገንዳ ተቆራርጠው በከረጢቶች ተሞልተው የተጣሉ ተጨማሪ የሴት የሰውነት ክፍሎችን ማግኘታቸውን ትላንት ቅዳሜ አስታውቀዋል።

ከትላንት በስተያ ዓርብ ሙኩሩ በተባለው የናይሮቢ የድሆች መኖሪያ አካባቢ በሚገኝ የቆሻሻ ማስወገጃ ቢያንስ የስድስት ሴቶች አካላት ተቆራርጠው በከረጢት ተጥለው ሲንሳፈፉ ከተገኙ ወዲህ ፖሊሶች ስፍራውን ሲያስሱ የቆዩ ሲሆን ትላንት ሌሎች የተቆራረጡ የሴት አካላት የሉባቸው አምስት ከረጢቶች አግኝተዋል።

ጉዳዩ የሀገሪቱን ሕዝብ በእጅጉ ማሸበሩ እና ማስቆጣቱ ተመልክቷል። ባለፈው ዓመት ኬኒያ ውስጥ የህንድ ውቂያኖስ ጠረፍ አካባቢ በሚገኝ ደን ብዙ መቶ "በረሃብ መሞት ያጸድቃል" የሚል ዕምነት ሰባኪ ተከታዮች አስከሬኖች የተቀበሩበት መቃብር መገኘቱ ህዝቡን እንዳሸበረ ይታወሳል።

ሰሞኑንም በመንግሥት ተቃዋሚ ስልፎች ላይ ብዛት ያላቸው ሰዎች መገደላቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ የሕግ አስከባሪ አካላት ከመጠን ያለፈ ኀይል በመጠቀም በመብት ቡድኖች ተወንጅለዋል።

በሙኩሩው የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ገንዳ አካባቢ ውጥረቱ ማየሉን የገለጹ ዘገባዎች ፖሊስ በቁጣ የወጡ ነዋሪዎችን ለመበተን ወደ ሰማይ ጥይት መተኮሱን አመልክተዋል።

ነጻ የፖሊስ ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን የተባለ ተቋም በአሰቃቂው ድርጊት የፖሊስ እጅ ይኖርበት እንደሆን በመመርመር ላይ መሆኑን ዓርብ ዕለት አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG