በሩዋንዳ ከጎርጎርሳዊያኑ 2000 አንስቶ ሀገሪቱን ሲመሩ የቆዩት ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜ በመጭው ሰኞ እንደሚያሸንፉ ቢጠበቅም ሦስት እጩዎች ግን እየተወዳደሩ ነው። ካጋሜ በቅርቡ ባደረጉት የምረጡኝ ቅስቀሳ ደጋፊዎቻቸውን ብዙ ነገሮች ቢደረጉም በድጋሚ ከተመረጡ ግን ሌሎች ተጨማሪ ሊሰሯቸው የሚችሏቸውን ነገሮች መኖራቸውን ተናግረዋል።
ካጋሜ በኪንያሩዋንዳ ቋንቋ ባደረጉት ንግግር “እኛ መንገዶች፣ ኤሌክትሪክ እና ሌሎች በርካታ መሰረተ ልማቶች አሉን” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “ነገር ግን ከመጭው ሰኞ ሐምሌ 8/ 2016 ምርጫ አንስቶ በእናንተ እርዳታ አሁንም የበለጠ ማሳካት እንፈልጋለን” ብለዋል።
የ66 ዓመቱ የሩዋንዳ የአርበኞች ግንባር መሪ ፖል ካጋሜ የአሁን ምርጫ በቀላሉ እንደሚያሸንፉ ይጠበቃል። ይሁን እንጂ ተቺዎች ይሄ ሊሆን የቻለው ፕሬዚዳንቱ ተቃውሞዎችን በማፈናቸውን እና በጉልበት በመግዛታቸው ነው ይላሉ።
መድረክ / ፎረም