በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል የሀማስ ወታደራዊ ሃላፊን በጥቃቱ ዒላማ አድርጌያለሁ አለች


የእስራኤል ጥቃት በካኻን ዩኒስ እና ጋዛ ሐምሌ 06/ 2016 ዓ.ም
የእስራኤል ጥቃት በካኻን ዩኒስ እና ጋዛ ሐምሌ 06/ 2016 ዓ.ም

የእስራኤል ጦር የሬዲዮ መገናኛ በካኻን ዩኒስ እና በጋዛ የተፈጸሙት ወታደራዊ ጥቃቶች የሀማስ ወታደራዊ ሃላፊ ላይ ያነጣጠሩ ናቸው አለ። በጥቃቱ 20 ፍልስጤማዊያን ህይወታቸው ማለፉን የሰርጡ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሰራዊቱ የሬዲዮ መገናኛ ክፍል አክሎ፤ የሀማስ ወታደራዊ ሃላፊ ሞሃመድ ዴፍ መሞቱ ግልጽ አይደለም ሲልም አስታውቋል።

የእስራኤል የጦር ሰራዊት ሪፖርቱን እየተመለከትኩ ነው ያለ ሲሆን፤ በአንጻሩ የጋዛ የጤና ሚኒስቴር 20 ግለሰቦች ሲሞቱ በተጨማሪ 90 ሰዎች መቁሰላቸውን በመግለጫው አስታውቋል። ይሁን እንጂ መግለጫው ወደ ሌሎች ሆስፒታሎች የሄዱ ሰዎችን አሃዝ አላካተተም። በሃማስ የሚመራ አንድ መገናኛ ብዙሃን በጥቃቱ ጉዳት የደረሰባቸው እና የሞቱት ሰዎች፤ ሲቪል የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችን ጨምሮ በትንሹ 100 ይደርሳሉ ሲል ዘግቧል።

ከፍተኛ የሃማስ ሹማምንቶች ሞሃመድ ዴፍ በህይወት መኖሩን እስካሁን ድረስ አላስታወቁም። በጥቅምት ወር ላይ በሃማስ ታጣቂ ቡድን የተመራ እና 1200 ሰዎችን ገድሎ 250 ሰዎችን ያገተው የሀማስ ተልዕኮ በኋላ፤ እስራኤል እያካሄደች ባለው የመልሶ ማጥቃት እስካሁን ድረስ 38 ሺህ ፍልስጤማዊያን ህይወታቸው ማለፉን የጋዛ የጤና ቢሮ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG