በትምህርት ጥራት እና በተሻለ የትምህርት አሰጣጥ ላይ የሚሠራው ገባሬ ሠናዩ “አይዞን ፋውንዴሽን”፤ በኢትዮጵያ ከዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ጋራ በመኾን ለሦስት ወራት ሲሰጥ የቆየውን “ሺ ካን” (ትችላለች) የተሰኘውን የወጣት ተመራቂ ሴት ተማሪዎች መርሐ ግብሩን ከሰሞኑ አጠናቋል።
የመርሐ ግብሩ ተሳታፊ ሴቶች፣ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ትምህርታቸውን በ2015 ዓ.ም. አጠናቀው የተመረቁ ሲኾኑ፣ በሥራ ትስስር፣ በሥራ ፈጠራ እና በሥራ ፍለጋ ክህሎት ሥልጠናዎችን ወስደዋል።
በመርሐ ግብሩ ማብቂያ ላይ፣ የሥራ ፈጠራ ሐሳቦቻቸውን ካጋሩት የተለያዩ ቡድኖች መካከል፣ አንዱ ቡድን የ1ነጥብ5 ሚሊዮን ብር የሥራ ማስጀመሪያ ተሸላሚ ኾኗል።
ኤደን ገረመው፣ ተሳታፊዎቹንና የአይዞን ፋውንዴሽን መሥራች እንዲሁም ሥራ አስፈጻሚ የኾኑትን ሻሎም ያቆብ ኣርአያን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።
መድረክ / ፎረም