የኔቶ አጋሮች በትላንትናው ዕለት ሩሲያ በዩክሬይን በምታካሂደው ጦርነት ቻይና የምትሰጠውን እገዛ እንድታቆም እና ኪቭ ኔቶን እንድትቀላቀል በሚያስችላት ጎዳና የማይታጠፍ ድጋፋቸውን ለመስጠት ቃል ገብተዋል። ይህም የዩክሬይንን የአየር ክልል የሚያስጠብቁ አዳዲስ ተዋጊ ጄቶች በዩክሬይን ሰማይ የሚበሩበትን ጊዜ ይጨምራል። በተያያዘ ዜና የኔቶ እና የዩክሬይን መሪዎች ዛሬ ሐሙስ ዋሽንግተን ላይ ተገናኝተው ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የአሜሪካ ድምጿ የፔንታገን ዘጋቢ ካርላ ባብ ያደረሰችንን ዘገባ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።