በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሱዳን ድንበር የለሽ የሐኪሞች ቡድኑ ሥራውን አቆመ


በሱዳን መዲና ካርቱም በሚገኘው የቱርክ ሆስፒታል የሕክምና አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን (MSF) እየተካሄደ ባለው ጦርነትና ሁከት ምክንያት ሥራውን ለማቆም መገደዱን አስታውቋል።

የቱርኩ ሆስፒታል በሱዳን መዲና አገልግሉት በመስጠት ላይ ያለ ብቸና ሆስፒታል ነበር። ቡድኑም ሕይወት አድን የሕክምና ሥራዎችን ሲያከናውን ነበር።

በጎ አድራጊው የሕክምና ቡድን ዓባላቱን ከሆስፒታሉ እንዳስወጣም አስታውቋል።

በሱዳን የድንበር የለሹ የሐኪሞች ቡድን መሪ የሆኑት ክሌር ኒኮሌት ውሳኔው ላይ በቀላሉ እንዳልተደረሰ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቀዋል።

ያለፈው አንድ ወር ለቡድኑ አስቸጋሪ እንደነበር ያወሱት መሪዋ፣ ታጣቂዎች ወደ ሆስፒታሉ በተደጋጋሚ በመግባት ተኩስ ከፍተዋል፣ በቡድኑ ዓባላትም ላይ ተኩስ የተከፈተበት ወቅት ነበር ሲሉ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG