በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

‘ኒውሮፓቲክ ፔይን’ ምንድነው?


‘ኒውሮፓቲክ ፔይን’ ምንድነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:43 0:00

በሕክምናው አጠራር በእንግሊዝኛ ‘ኒውሮፓቲክ ፔይን’ ይሰኛል። የተለያዩ መንስኤዎች ቢኖሩትም በአመዛኙ በነርቭ ሥርአት ላይ በሚደርስ ጉዳት የሚመጣ እና ብርቱ የሥቃይ ስሜት የሚያስከትል የበሽታ ዓይነት ነው።

“በውስብስብ ተፈጥሮው የተነሳ በምርመራ ጭምር ለማወቅ አዳጋች ሊሆን ይችላል” ይላሉ ከፍተኛ የነርቭ ሃኪሙ ዶ/ር እናውጋው መሃሪ።

እንደ ስኳር በሽታ አለያም ከአንድ ቦታ ተነስቶ ወደ ሌላ የሰውነት ክፍል የሚሰራጭ አለያም የሚጠዘጥዝ የሕመም ስሜት እንደሚያስከትል ያስረዱት ዶ/ር እናውጋው፣ አንዳንዴ የሕመም ሥሜቱ ያለበትን የሰውነት ክፍል በእጅ መንካት ብቻ ሥቃዩን ሊያብብስ እንደሚችል ያብራራሉ።

የሕክምናው ዋና አላማም የሥቃይ ስሜትን መቀነስ እና በሕመሙ ሳቢያ በዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ የሚያከተለውን የተመሳቀለ ሁኔታ ማሻሻል መሆኑን፤ በአጭሩም ሕመሙን ነጥሎ ከማከም ይልቅ ሕመምተኛው ያለበትን ጠቅላላ ሁኔታ ማጤን እና ለመርዳት መሞከር እንደሚበጅ ያስረዳሉ።

ዶ/ር እናውጋው መሃሪ በማዕከላዊ ደቡብ ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትሷ ቴነሲ ክፍለ ግዛት በሚገኘው ትራይስቴት ሆራይዘን ሆስፒታል የስትሮክ ሕክምና ፕሮግራም ኃላፊ ናቸው።

XS
SM
MD
LG