በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘንድሮ በዐማራ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኞች ቁጥር ዝቅተኛ መኾኑን ቢሮው ገለጸ


ዘንድሮ በዐማራ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ተፈታኞች ቁጥር ዝቅተኛ መኾኑን ቢሮው ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00

በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተሰጠ ባለው የ2016 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና፣ በዐማራ ክልል፣ ለፈተናው የተቀመጠው ተማሪ ቁጥር ከወትሮው ዝቅተኛ መኾኑን፣ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ዘንድሮ፣ በክልሉ ከ96ሺሕ በላይ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ መኾናቸውን የገለጹት ኃላፊው፣ በቀጠለው ግጭት ምክንያት ግን፣ በተለይ ከፍተኛ ቁጥር ይመዘገቡባቸው በነበሩ የምሥራቅ ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች የሚገኙ ተማሪዎች “ለፈተናው አልተቀመጡም፤” ብለዋል፡፡

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ቀደም ብሎ ባወጣው መግለጫ፣ ለዘንድሮው ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና እንዲቀመጡ ከታሰቡት ከ19ሺሕ በላይ የዞኑ ተማሪዎች ውስጥ፣ ፈተናውን የሚወስዱት፣ ከአምስት ትምህርት ቤቶች የተገኙ 577 ተማሪዎች ብቻ እንደሚኾኑ አስታውቆ ነበር፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት በምኅጻሩ ዩኒሴፍ፣ ትላንት ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርቱ ደግሞ፣ በዐማራ ክልል የቀጠለው ግጭት በፈጠረው ተጽእኖ ምክንያት፣ 4ሺሕ178 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ገልጿል። በምሥራቅ ጎጃም፣ በምዕራብ ጎጃም እና በደቡብ ጎንደር ዞኖች ከሚገኙት ትምህርት ቤቶች መካከል፣ 89 በመቶዎቹ ዝግ መኾናቸውን ዘገባው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG