በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ኦዴሳ ወደብ ላይ የሚሳይል ጥቃት አደረሰች


የአካባቢው ነዋሪ ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ የወደመው መኖሪያ ቤቱን ይመለከታል፤ ኪየቭ፣ ሐምሌ 9/2024
የአካባቢው ነዋሪ ጥቃቱ ከደረሰ በኋላ የወደመው መኖሪያ ቤቱን ይመለከታል፤ ኪየቭ፣ ሐምሌ 9/2024

ሩሲያ ኦዴሳ ወደብ ላይ ዛሬ ረቡዕ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ ሁለት ሰዎች መግደሏን የዩክሬይን ባለስልጣናት ተናገሩ፡፡

የዩክሬይን የጦር ኅይል እንዳለው ሩሲያ በዩክሬይን ዙሪያ በየቀኑ በቀጠለችው የአየር ጥቃት በዛሬው ጥቃቷ አምስት ሚሳይሎች እና ሃያ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ተጠቅማለች፡፡

የዩክሬይን የአየር ኅይል በሰጠው መግለጫ አስራ አራቱን ድሮኖች መትተን ጥለናል ብሏል፡፡ ድሮኖቹ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ዒላማ ያደረጉ እንደነበሩ የተናገሩት የዩክሬይን ባለስልጣናት በጥቃቱ በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ዩክሬነርጂዮ የተባለው የኤሌክትሪክ ኅይል ማሰራጫ በአንደኛው ጣቢያው ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን አመልክቷል፡፡ የሩሲያ የመከላከያ ሚንስቴር በበኩሉ ሁለት ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ቤልጎሮድ እና ቮሮኔዥ ክፍለ ግዛቶች ላይ መትተን ጥለናል ብለዋል፡፡

በተያያዘ ዜና በዋሽንግተን የዩክሬይን ፕሬዚደንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ የኔቶ አባል ሀገሮች ለሀገራቸው በተለይ በአየር መከላከያ የሚሰጡትን ድጋፍ ከፍ እንዲያደርጉ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ዜሌንስኪ ትላንት ማክሰኞ ባደረጉት ንግግር ሩሲያ ሰኞ ዕለት አርባ ሚሳይሎች በመተኮስ ኪቭ በሚገኝ የሕጻናት ሆስፒታል ላይ ጥቃት ማድረሷን አስመልክተው ተናግረዋል፡፡ በጥቃቱ በሀገሪቱ ዙሪያ ቢያንስ 43 ሰዎች ሲገደሉ 200 የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ዜሌንስኪ ገልጸዋል፡፡

የኔቶ አባል ሀገሮች በተለይም ዩናይትድ ስቴትስ ፈጣን እርምጃ እንድትወስድ ያሳሰቡት ዜሌንስኪ “ባለስልጣናቷ የሕዳሩን ምርጫ መጠበቅ የለባቸውም” ሲሉ አክለዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG