በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሃማስ የእስራኤል ታጋቾችን በተመለከተ ለመነጋገር የአሜሪካን ሀሳብ መቀበሉ ተነገረ


ምስሉ በእስራኤል የአየር እና የምድር ጥቃት የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በጋዛ ሰርጥ ደቡባዊዋ ካን ዮኒስ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ያሳያል ።
ምስሉ በእስራኤል የአየር እና የምድር ጥቃት የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በጋዛ ሰርጥ ደቡባዊዋ ካን ዮኒስ ከተማ ጎዳናዎች ላይ ያሳያል ።


በጋዛ ጦርነትን ለማስቆም ያለመ ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ከተጠናቀቀ ከ16 ቀናት በኋላ ሀማስ ወታደሮችን እና ወንዶችን ጨምሮ የእስራኤል ታጋቾችን በሚለቅበት ሁኔታ ዙሪያ ንግግር ለመጀመር የአሜሪካን ሀሳብ መቀበሉን አንድ ከፍተኛ የሀማስ ምንጭን ጠቅሶ ሮይተርስ በዛሬው ዕለት ዘግቧል ።

ታጣቂው እስላማዊ ቡድን እስራኤል ከፊርማ በፊት አስቀድማ ተኩስ ለማቆም ማረጋገጫ ትስጥ የሚለውን ቅድመ ሁኔታውን ያነሳ ሲሆን ፣ በመጀመሪያው ምዕራፍ ስድስት ሳምንታት ውስጥ ለውጤት ይበቃ ዘንድ ድርድሮችን መፍቀዱን ማንነታቸው በሚስጢር እንዲያዝ የጠየቁት የሮይተርስ ምንጭ ተናግረዋል ።

ለዓለም አቀፍ የሽምግልና የሰላም ጥረቶች ቅርበት ያላቸው የፍልስጤም ባለስልጣን ሃሳቡ በእስራኤል ተቀባይነት ካገኘ ወደ ስምምነት ማዕቀፍ ሊያመራ እንደሚችል እና በእስራኤል እና በሃማስ መካከል በጋዛ ለዘጠኝ ወራት የቆየውን ጦርነት ሊያስቆም እንደሚችል ተናግረዋል ።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የእስራኤል ተደራዳሪ ቡድን ምንጭ፣ አሁን ስምምነት ላይ ለመድረስ የሚያስችል ዕድል እንዳለ ተናግረዋል። ይህ በጋዛ ለዘጠኝ ወራት በዘለቀው ጦርነት ወቅት ከታዩት አቋሞች በእጅጉ የተለየ ሆኗል ። እስራኤል በሃማስ የተቀመጡት ቅደመ ሁኔታዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ስትገልጽ ቆይታለች ።
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ቃል አቀባይ ዛሬ ቅዳሜ፣ በአስተያየት እንዲሰጡ ለቀረበላቸው ጥያቄ ወዲያውኑ ምላሽ አልሰጡም። አርብ ዕለት ፅህፈት ቤታቸው በሚቀጥለው ሳምንት ንግግሮች እንደሚቀጥሉ ገልጾ አሁንም በሁለቱ ወገኖች መካከል ክፍተቶች እንዳሉ አፅንዖት ሰጥቷል።

ሃማስ በደቡባዊ የእስራኤል ከተሞች ላይ ጥቅምት 7 ቀን ጥቃት ከደረሰ በኋላ እና የእስራኤል ባለስልጣን አሃዞች መሰረት 1,200 ሰዎችን ከገደለ ፣ 250 ያህሉን ባገተ ማግስት በቀሰቀሰው ግጭት የጋዛ የጤና ባለስልጣናት እንደሚገልጹት ፣ እስከ አሁን ከ38,000 በላይ ፍልስጤማውያንን ህይወት ተቀጥፏል ።

አዲሱ የሰላም ሀሳብ ፣ ሸምጋዮች ጊዜያዊ የተኩስ አቁም፣ የእርዳታ አቅርቦት እና የእስራኤል ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ ዋስትና እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ ነው ሲል የሃማስ ምንጭ ገልጸዋል) ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG