በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

FERTILIZER SHORTAGE IN TIGRAI.mp3


FERTILIZER SHORTAGE IN TIGRAI.mp3
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00

በትግራይ ክልል፣ በአፈር ማዳበሪያ እና በፀረ ተባይ ኬሚካል አቅርቦት ከፍተኛ ውስንነት እንደሚታይ ያመለከቱ አርሶ አደሮች፣ ጦርነት እና ድርቅ ካስከተሉባቸው ችግሮች በተጨማሪ በግብአት እጥረቱ የመኸር ወቅት ምርታማነቸው እንዳይጎዳ ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

በክልሉ የአፈር ማዳበሪያ ስርጭቱ ከሚያስፈልገው በእጅጉ ያነሰ እንደኾነ የገለጸው ተቃዋሚው ሣልሳይ ወያኔ ፓርቲም፣ አሳሳቢ ሲል የገለጸውን የማዳበሪያ እጥረት በአፋጣኝ ለመቅረፍ፣ የረድኤት ድርጅቶች የበኩላቸውን እገዛ እንዲያደርጉ ባወጣው መግለጫ ጠይቋል፡፡

የክልሉ የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ በበኩሉ፣ እስከ አሁን ከ430ሺሕ ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ወደ ክልሉ መግባቱን አስታውቆ፣ “አቅርቦቱ ካለፉት ዓመታት የበለጠና መሻሻል የታየበት ነው” ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG