በትጥቅ ትግል ላይ ያሉ ዐማፅያን ኀይሎች፣ በማንኛውም ጊዜ ወደ ንግግር ለመምጣት ከፈለጉ መንግሥታቸው ዝግጁ መኾኑን፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ተናግረዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በኢትዮጵያ ያሉ ግጭቶችን ጨምሮ ዛሬ ሐሙስ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለተነሡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከሶማሊያ ጋራ የተፈጠረውን አለመግባባት በውይይት ለመፍታት ዝግጁ ስለመኾናቸውም በድጋሚ አብራርተዋል፡፡