በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀጠለው የኬንያውያን ተቃውሞ እና የባለሞያዎች ትንታኔ


የቀጠለው የኬንያውያን ተቃውሞ እና የባለሞያዎች ትንታኔ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:38 0:00

በኬንያ፣ አወዛጋቢ በኾነው የፋይናንስ ሕግ ረቂቅ ላይ ተቃውሞ መነሣቱን ተከትሎ፣ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በምክር ቤቱ በጸደቀው የሕጉ ረቂቅ እንደማይፈርሙ ቢያስታውቁም፣ ተቃውሞው ግን አሁንም ቀጥሏል፡፡

ከተቃውሞ እንቅስቃሴው ጋራ በተያያዘ እስከ አሁን 39 ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የተባበሩት መንግሥታት የጋራ ልዩ መርሐ ግብር በተባለ ተቋም፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ላይ የሚሠሩት አቶ ጌታቸው ተክለ ማርያም፣ ኬንያውያን፥ በሌሎች ሀገራት ተጽእኖ ሥር ወድቋል፤ በሚሉት የሩቶ መንግሥት ላይ እምነት ማጣታቸው፣ ለተቃውሞው መቀጠል ምክንያት ስለመኾኑ ያስረዳሉ፡፡

ኬንያ፣ ከፍተኛ የዕዳ ጫና ካለባቸው ሀገራት አንዷ መኾኗን የሚጠቅሱት የፋይናንስ እና ምጣኔ ሀብት ባለሞያው ዶክተር አብዱልመናን ሙሐመድ፣ ለተቃውሞው መነሻ የኾነው የፋይናንስ ሕግ፣ ጫናውን ለማስተካከል በአበዳሪ ተቋማት ከሚሰጥ ምክረ ሐሳብ መመንጨቱን ያመለክታሉ፡፡

XS
SM
MD
LG