በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በማረቆ ልዩ ወረዳ እና በምሥራቅ ጉራጌ ዞን-መስቃን ወረዳ አዋሳኝ አካባቢ፣ እንደቀጠለ በተገለጸው የታጣቂዎች ጥቃት፣ ተጨማሪ አራት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች አራት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን፣ ነዋሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ፡፡
በጉዳዩ ላይ፣ ከምሥራቅ መስቃን ወረዳ እና ከማረቆ ልዩ ወረዳ፣ እንዲሁም ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባለሥልጣናት ምላሽ እና አስተያየት ለማካተት ያደረገነው ጥረት፣ ባለሥልጣናቱ ስልካቸውን ስለማያነሡ አልተሳካም፡፡
የአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የጠየቃቸው የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁር፣ የሕዝብ ጥያቄ በወቅቱ ተገቢውን ምላሽ ባለማግኘቱ ጉዳቱ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡