የቀድሞዋ ይዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ካሮላይና ክፍለ ግዛት አገረ ገዢ ኒኪ ሄሊ ከፕሬዝደንታዊ ምርጫው ዕጩ ተፎካካሪነት ከወጡ ረጅም ጊዜ ቢሆናቸውም አሁንም የሪፐብሊካን መራጮችን ድጋፍ መሳባቸውን ቀጥለዋል።
የአሜሪካ ድምጿ ዶራ ሜኩዋር ባጠናቀረችው ዘገባ በመጪው ምርጫ ከፕሬዝደንት ጆ ባይደን እና ከቀድሞው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትረምፕ ማንኛቸው እንደሚያሸንፉ የኒኪ ሄሊ ደጋፊዎች ድምጽ እንዴት ሊወስን እንደሚችል ትዳስሳለች።