በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቤት ኪራይ ቁጥጥር ዐዋጅ ትግበራ ለማኅበራዊ መስተጋብር ጥንቃቄ እንዲደረግ ተጠየቀ


please wait

No media source currently available

0:00 0:09:05 0:00

“የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር ዐዋጅ” መውጣቱን ተከትሎ፣ ቤት ልቀቁ በሚሉ አከራዮች ጫና እየደረሰባቸው መኾኑን፣ ተከራዮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

በዐዲስ አበባ ከተማ እየተካሔደ የሚገኘው የተከራይ እና አከራይ ውል ስምምነት ምዝገባ፣ የኪራይ ዋጋንና የተከራይን የቆይታ ጊዜ የሚወስን እንደኾነ በዐዋጁ ላይ ተገልጿል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ፣ ዐዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ፣ በሕግ ከተቀመጠው አሠራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ጭማሬ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ መከልከሉን አስታውቋል፡፡

በዐዋጁ ላይ አስተያየት የሰጡ የማኅበራዊ ሳይንስ ባለሞያዎች ደግሞ፣ ሕጎች ሲወጡ በሕዝቡ ማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ጫና እንደማይፈጥሩ ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG