በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑቲን መካከለኛ የኑክሌር አቅም ያላቸውን ሚሳኤሎች መመረታቸው እንዲቀጥል ጥሪ አቀረቡ


የሩሲያው ፕሬዘዳንት ሚካኤል ጎርባቾቭ እና የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሮናልድ ሬገን እ.ኤ.አ ታህሳስ 8/1987
የሩሲያው ፕሬዘዳንት ሚካኤል ጎርባቾቭ እና የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ሮናልድ ሬገን እ.ኤ.አ ታህሳስ 8/1987

የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር በተደረገ እና አሁን በተፋቀ ስምምነት መሰረት፤ ታግደው የቆዩት የአጭር እና የመካከለኛ ርቀት ተወንጫፊ አቅም ያላቸው ሚሳኤሎች መመረታቸው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመካከለኛ ርቀት የኑክሌር ኃይሎች ስምምነት መሰረት በጎርጎርሳዊያኑ 1987 በሚካኤል ጎባቾቭ እና በሮናልድ ሬገን መካከል በተደረገ ውል ሁለቱ ልዕለ ሃያላን ሀገሮች ከ500 እስከ 5,500 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ የሚወነጨፉ የኒውክሌር እና መደበኛ ሚሳኤሎችን ማምረት ለማቆም ተስማምተዋል።

በስምምነቱ መሰረት ዩናይትድ ስቴትስ እና ሩሲያ 2,692 የአጭር፣ እና የመካከለኛ ርቀት ሚሳኤሎችን በጎርጎሮሳዊያኑ ሰኔ 1 ቀን 1991 የትግበራው የመጨረሻ ቀን ድረስ ማውደማቸውን የጦር መሳሪያ ቁጥጥር ማኅበር አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ከጎርጎርሳዊያኑ 2014 አንስቶ ዩናይትድ ስቴትስ ሩሲያ ስምምነቱን እያከበረች አይደለም በማለት በተደጋጋሚ የከሰሰች ሲሆን፤ ሩሲያ ክሱን ስታጣጥል ቆይታለች።

ይህን ተክትሎም የቀድሞው ፕሬዘዳንት ትራምፕ አስተዳደር በጎርጎርሳዊያኑ 2019 ሩሲያ ውሏን አላካበረችም ቻይናም ሚሳኤል በማከማቸት ላይ ናት የሚል ስጋት በመጥቀስ፤ ከስምምነቱ መውጣቱን አስታቋል።

ፑቲን ትላንት አርብ በቴሌቪዥን በተላለፈው የሩሲያ የፀጥታው ምክር ቤት ስብሰባ ላይ፤ አሜሪካ ሚሳኤሎቹን በማምረት ወደ ዴንማርክ እና ፊሊፒንስ በመላኳ፤ ሚሳኤሎቹን እንደገና ማምረት መጀመራችን አሁን አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ጦር በዚህ ዓመት ሚያዝያ ወር ለወታደራዊ ልምምድ አካል መካከለኛ የመወንጨፍ አቅም ያላቸው ሚሳኤሎች ወደ ሰሜናዊ ሉዞን፣ ፊሊፒንስ በተሳካ ሁኔታ ማሰማራቱን ማስታውቁ ይታወሳል።

ፑቲን በትላንትናው ዕለት ባደረጉት ንግግርም “ባለው ነባራዊ ሁኔታ እነዚህ የማጥቂያ ስርዓቶች ማምረት መጀመር አለብን፤ አስፈላጊ ሲሆን ደህንነታችን ለመጠበቅ እንጠቀምባቸዋል” ብለዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG