በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጋዛ ነዋሪዎች  “በማይቋቋሙት” ሁኔታ ውስጥ እየኖሩ ነው ሲል ተመድ አስታወቀ


ጋዛ ሰኔ 21/ 2016 ዓ.ም
ጋዛ ሰኔ 21/ 2016 ዓ.ም

የመንግስታቱ ድርጅት የረድኤት ተቋም ለጋዛ ቃል አቀባይ ሉዊስ ዋተርሪጅ ትላንት አርብ የጋዛ ነዋሪዎች በቦምብ በወደሙ ህንፃዎች አሊያም መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ከፍርስራሽ እና ቆሻሻዎች ጎን ለመኖር ተገደዋል ሲሉ ተናግረዋል። ዋተርሪጅ ሁኔታውን ‘እጅግ አስከፊ’ ሲሉም ጠርተውታል።

ከአራት ሳምንታት በኋላ ረቡዕ ዕለት ወደ ጋዛ የተመለሱ ዋተርሪጅ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የአካባቢው ኑሮ ‘ጉልህ በሆነ መልኩ አሽቆልቁሏል’ ሲሉ ብለዋል።

ቃል አቀባይዋ ከተጀመረ ዘጠኝ ወራት ባስቆጠረው ጦርነት የጋዛ ሰርጥ ወድሟል ሲሉም ተናግረዋል። ህንጻዎች እና መኖርያ ቤቶች በመውደማቸውም ሰዎች በየቦታው ለመጸዳዳት መገደዳቸው ተገልጿል።

ዋተርሪጅ የጋዛ ረድኤት ደህነቱ ተጠብቆ እንዲዳረስ የነዳጅ ዘይት አቅርቦት እንዲኖር የማድረግ ተግዳሮት መኖሩን አክለው አስታውቀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG