በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ2024 ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ሪፖርት እና የኢትዮጵያ ድርሻ


 የ2024 ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ሪፖርት እና የኢትዮጵያ ድርሻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:13 0:00

የኢትዮጵያ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በ11 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን፣ የተባበሩት መንግሥታት ንግድ እና ልማት ኮንፈረንስ አስታወቀ፡፡

ተቋሙ ይፋ ባደረገው፣ የ2024 ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ በ2023 የሳበችው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ 3ነጥብ26 ቢሊዮን ዶላር እንደኾነ ገልጿል፡፡

ይህም፣ ካለፈው ዓመት አንጻር ቅናሽ ቢኖረውም፣ በምሥራቅ አፍሪካ ግን ከፍተኛው እንደኾነ አመልክቷል፡፡

የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት ባለሞያዎች በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ ያገኘችው የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ አሁን ካለችበት ኹኔታ አንጻር “ከፍተኛ የሚባል መኾኑን” አስረድተዋል፡፡

ለተሻሻለ ውጤት ምክንያቱም፣ ኢኮኖሚውን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት የሚያደርጉ የመንግሥት የፖሊሲ ማሻሻያዎች ሊኾኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

XS
SM
MD
LG