የ2024ቱ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ የመጀመሪያ ክርክር ነገ ኀሙስ ይካሔዳል።
ለዚኽ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያው ይኹን እንጂ፣ እጩዎቹ ግን በዚኽ መሰሉ መድረክ ተገናኝተው ሲከራከሩ የመጀመሪያቸው አይደለም።
የአሜሪካ ድምፅዋ ከፍተኛ የዋሽንግተን ዘጋቢ ካሮሊን ፐርሱቲ፣ በነገው የፕሬዚዳንት ጆ ባይደንና የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ክርክር፣ ልናይ እና ልንሰማ ስለምንችላቸው ነገሮች አንዳንድ ፍንጮችን ፍለጋ ወደ 2020’ው ክርክራቸው ትወስደናለች። አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።