በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የባሕር ዳር የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጠየቁ


የባሕር ዳር የሰላም ኮንፈረንስ ተሳታፊዎች የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00

በትጥቅ ግጭት ውስጥ በሚገኘው የዐማራ ክልል ርእሰ መዲና ባሕር ዳር ከተማ፣ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሔደውን የሰላም ጉባኤ የተሳተፉ ልዩ ልዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች፣ በግጭቱ ዐውድ ውስጥ የታሰሩ ፖለቲከኞች፣ ምሁራን፣ ጋዜጠኞች እና ተጽእኖ ፈጣሪ ዜጎች እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

ተሳታፊዎቹ፣ በሰላም ጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ባወጡት ባለዐሥር ነጥብ የአቋም መግለጫ፣ መንግሥት ታሳሪዎቹን በምሕረት እና በይቅርታ መፍታቱ፣ “ለክልሉ ዘላቂ ሰላም የበኩላቸውን እንዲወጡ ያስችላል፤” ብለዋል፡፡

ጉባኤውን በአዘጋጀው በክልሉ መንግሥት እና በተሳታፊዎች መካከል፣ እስረኞቹ እንዲፈቱ መግባባት ላይ ስለመደረሱ ግን የተገለጸ ነገር የለም፡፡

የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ፣ በሰላም ጉባኤው የአቋም መግለጫ ላይ የቀረበው ጥያቄ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በዐማራ ክልል ላይ የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ፣ ባለፈው ግንቦት ወር መጨረሻ ማብቃቱን አስመልክቶ ያወጣውን መግለጫ እንደሚያንጸባርቅ፣ በኮሚሽኑ የሪጅን ዲሬክተር አቶ ዓለሙ ምሕረት አመልክተዋል፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ/አብን/ ፓርቲን በመወከል ከክልሉ ተመርጠው ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የገቡት አቶ አበባው ደሳለው፣ መንግሥት ራሱ ባዘጋጀው የምክክር መድረክ ላይ የግጭት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቅ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ፣ ታሳሪዎችን ለመፍታት ዕቅድ እንዳለው የሚያሳይ ነው፤ ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG