በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሳ ክፍያ የዐዋጅ ማሻሻያው “የመብት ጥሰትን ያስከትላል” ሲል ኢሰመኮ ተቸ


 የካሳ ክፍያ የዐዋጅ ማሻሻያው “የመብት ጥሰትን ያስከትላል” ሲል ኢሰመኮ ተቸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:49 0:00

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ትላንት ማክሰኞ የጸደቀው፣ የመሬት ይዞታ ካሳ ክፍያ የዐዋጅ ማሻሻያ፣ የመብት ጥሰትን ያስከትላል፤ ሲል ተችቷል፡፡

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበትን፣ ካሳ የሚከፈልበትንና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ኹኔታ የሚወስነው የዐዋጁ ማሻሻያ፥ የካሳ ክፍያን፣ ከፌዴራሉ መንግሥት ወደ ክልሎች እና የከተማ አስተዳደሮች ማሸጋገርን ጨምሮ ከዳኝነት ጉዳዮች ጋራ የተገናኙ ለውጦችንም ደንግጓል፡፡

ይህም በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ አሥነስቷል፡፡

ማሻሻያው፣ በቀድሞው ዐዋጅ ላይ ያሉ ለባለይዞታዎች ጠቃሚ የኾኑ ድንጋጌዎችን ወደ ኋላ ይመልሳል፤ ሲሉ፣ የኢሰመኮ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ሥራ ክፍል ዲሬክተር ዶር. ብራይትማን ገብረ ሚካኤል ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG