በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋግኽምራ ዞን 15 ሕፃናት በኩፍኝ ወረርሽኝ ሕይወታቸው ማለፉን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ


 በዋግኽምራ ዞን 15 ሕፃናት በኩፍኝ ወረርሽኝ ሕይወታቸው ማለፉን ጽሕፈት ቤቱ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:50 0:00

በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን መደበኛ ክትባት በመቋረጡ በተከሠተው የኩፍኝ ወረርሽ፣ ባለፈው ወር ብቻ 15 ሕፃናት መሞታቸውን፣ የዞኑ ጤና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ፣ ዛሬ ማክሰኞ ለአሜሪካ ድምፅ እንደገለጹት፣ በአካባቢው በተደጋጋሚ ባጋጠመው የጸጥታ ችግር የተነሣ ሕፃናት በዕድሜያቸው ማግኘት የነበረባቸውን መደበኛ ክትባት አላገኙም።

ከአምስት ወራት በፊት በሰሀላ ሰየምት ወረዳ ብቻ ተከሥቶ የነበረው የኩፍኝ ወረርሽኝ በኹሉም ወረዳዎች በመስፋፋቱ፣ በአሁኑ ሰዓት ሁለት ሺሕ ሕፃናት በወረርሽኙ መያዛቸውን ገልጸዋል። በቅርቡ፣ ለሕፃናቱ በዘመቻ መልክ የክትባት አገልግሎት እንደሚጀመር የጠቆሙት ኃላፊው፣ በጸጥታው ችግር የተነሣ ለባለሞያዎች ተደራሽነት አዳጋች በኾኑ ወረዳዎች ያሉ ሕፃናትን ለመታደግም ረጂ ድርጅቶች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG