በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሐብሩ ወረዳ የተኩስ ልውውጥ ባልታጠቁ ነዋሪዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ነዋሪዎች አስታወቁ


በሐብሩ ወረዳ የተኩስ ልውውጥ ባልታጠቁ ነዋሪዎች ላይ ሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱ ነዋሪዎች አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:37 0:00

በሰሜን ወሎ ዞን ሐብሩ ወረዳ ውርጌሳ ከተማ አካባቢ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ በመከላከያ ኀይል እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በነበረ የተኩስ ልውውጥ፣ ባልታጠቁ ሰዎች ላይ የሞት እና የአካል ጉዳት መድረሱን ነዋሪዎች አስታወቁ።

በከተማው የጸጥታ ችግር እንደነበርና የተጎዱም ሰዎች መኖራቸውን የጠቀሰው የሐብሩ ወረዳ አስተዳደር፣ አኀዛዊ መረጃ ለመስጠት ግን በምርመራ ላይ መኾኑን ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል፡፡

ከውርጌሳ ከተማ በተጨማሪ፣ በተለያዩ የሐብሩ ወረዳ አቅራቢያዎችም የጸጥታ ችግር እንደሚስተዋል የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው ሑሴን መሐመድ፣ በሕዝቡ ዕለታዊ ኑሮ ላይ ጫና መፍጠሩን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG