በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ አምስት አስክሬን ሲገኝ 68 ስደተኞችን በህይወት ማትረፍ ተቻለ


የትሪኒዳድ እና ቶባጎ አሳ ደሴት አጥማጆች ባህላዊ ጀልባ 2014 ዓ.ም
የትሪኒዳድ እና ቶባጎ አሳ ደሴት አጥማጆች ባህላዊ ጀልባ 2014 ዓ.ም

የስፔን የባህር ላይ ነፍስ አድን ተቋም አንዲት በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ስትጓዝ የነበረች መርከብ፤ በካናሪ ደሴቶች አካባቢ በባህላዊ የአሳ ማጥመጃ ጀልባ ሆነው ሲንሳፈፉ የነበሩ 68 ስደተኞችን በህይወት መታደጓን ሀሙስ ዕለት አስታውቋል። የነፍስ አድን ተቋሙ በተጨማሪም በጀልባዋ ውስጥ አምስት አስከሬን መገኘታቸውንም ጨምሮ ገልጿል።

ከሰሜን ምዕራን ስፔን ወደ ብራዚል በመጓዝ ላይ የነበረው የነዳጅ ዘይት ተሸካሚ መርከብ ረቡዕ እለት በካናሪ ካሉት ሰባት ደሴቶች መካከል አንዷ በሆነቸው በቴንሪፌ ደቡባዊ አቅጣጫ 815 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ጀልባዋ ስትንሳፈፍ ማየታቸውን ገልጸዋል።

ባህላዊ ጀልባዋ በሴኔጋል እና በሞሪታኒያ አሳ አጥማጆች ጥቅም ላይ የምትውል መሆኗም ተገልጿል። በነፍስ አድን መርከቧ ውስጥ ከነበሩ ተጓዦች መካከል አንዱ የሆነው ስቲቭ ዲልቤክ ሰዎቹ በውቅያኖሱ ላይ ሲንሳፈፉ 20 ቀናት መቆየታቸውን ተናግረዋል ሲል ለአሶሽየትድ ፕሬስ የዜና አውታር አስታውቋል። ከተጓዦቹ መካከል 62 ወንዶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ሴቶች እና ህጻናት መሆናው ነው የተነገረው።

የስፔን የነፍስ አድን ተቋሙ በኢሜል በላከው መግለጫ መርከቧ ሳንታ ክሩዝ ቴንሪፌ ወደብ ትላንት አርብ እንደምትደርስ ገልጿል። የስፔን የሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ባለፈው የጎርጎሮሳዊያኑ ዓመት 55,618 ስደተኞች ወደ ካናሪ ደሴቶች በጀልባ መምጣታቸውን አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG