በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በ2011 ከነበረበት ከስድስት በመቶ በላይ ማደጉን መንግሥት ገለጸ


የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በ2011 ከነበረበት ከስድስት በመቶ በላይ ማደጉን መንግሥት ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:11 0:00

ባለፉት አምስት ዓመታት የተካሔደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር፣ ውጤት እያስገኘ መኾኑን የገለጸው የኢትዮጵያ መንግሥት፣ በዚኽም የአገሪቱ የደን ሽፋን፥ በ2011 ዓ.ም. ከነበረበት 17ነጥብ2 በመቶ አሁን ላይ 23ነጥብ6 መድረሱን አስታውቋል።አገሪቱ በዘንድሮው ክረምትም፣ 7ነጥብ5 ቢሊዮን የሚቆጠሩ ችግኞችን ለመትከል ማቀዷን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ከስድስት ዓመታት በኋላም የደን ሽፋኑን ወደ 30 በመቶ የማድረስ ትልም መኖሩን ጠቁመዋል

በተከታታይ የተካሔዱት የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሮች፣ ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ ያመለከቱት የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው አንድ የዘርፉ ባለሞያ ደግሞ፣ የደን ሽፋኑ አድጓል የተባለበት መጠን ግን፣ ማጣራት ሊያስፈልገው እንደሚችል እምነታቸውን አመልክተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG