በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች እየታየ ባለው የእንስሳት በሽታ አራት ሰዎች ሞቱ


በትግራይ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች እየታየ ባለው የእንስሳት በሽታ አራት ሰዎች ሞቱ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:21 0:00

በትግራይ ክልል፣ አንትራክስ ወይም በልማድ አባ ሰንጋ በተባለው የእንስሳት በሽታ፣ አራት ሰዎች መሞታቸውን፣ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። በበሽታው የተያዘን የበሬ ሥጋ የተመገቡ ሌሎች ሰዎችም መታመማቸው ታውቋል።

በክልሉ በጦርነቱ ወቅት ተቋርጦ ከቆየው የእንስሳት ክትባት ጋራ በተያያዘ፣ በሽታው በተለያዩ የክልሉ ወረዳዎች መስፋፋቱ ተገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት የበሽታው ክትባት ወደ ክልሉ እየገባ እንደሚገኝ የተጠቆመ ሲኾን፣ ሣር በል የቤት እንስሳትን በወቅቱ ማስከተብ እንደሚገባ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG