በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የሚኖሩ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ጠየቁ


በኢትዮጵያ የሚኖሩ ስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች አገልግሎቶች እንዲሻሻሉ ጠየቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:22 0:00

በኢትዮጵያ ያሉ ስደተኞች፣ ከአገልግሎት አቅርቦት እና ከጸጥታ ጋራ የተያያዙ ችግሮች እንዲፈቱላቸው ጥሪ አቀረቡ።

በሰሜን ጎንደር ዞን በዓለምዋጭ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፣ ባለፈው ማክሰኞ፣ በአካባቢያቸው፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል የተኩስ ልውጥ ተደርጎ፣ አንድ ስደተኛ በበራሪ ጥይት መቁሰሉን ገልጸው፣ በኹኔታው ስጋት እንዳደረባቸው ተናግረዋል፡፡

በምዕራብ ጎንደር ዞን ያሉት የሱዳን ስደተኞች ደግሞ፣ የጸጥታ እና የአገልግሎት አቅርቦት ችግሮች እንዳሉባቸው ጠቅሰው፣ የሚመለከታቸው አካላት ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟሉ ጠይቀዋል፡፡

ዛሬ እየተከበረ ያለውን “የዓለም ስደተኞች ቀን”ን በማስመልከት መግለጫ ያወጣው፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በበኩሉ፣ በስደተኞች አገልግሎት ላይ የሚታዩት ክፍተቶች እንዲስተካከሉ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG