በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓድዋ ከተማ ታግታ ደብዛዋ የጠፋው አዳጊ መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ


በዓድዋ ከተማ ታግታ ደብዛዋ የጠፋው አዳጊ መገደሏን ፖሊስ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:11 0:00

በትግራይ ክልል በዓድዋ ከተማ፣ ከሦስት ወራት በፊት በአጋቾች ተይዛ የቆየችው አዳጊ ማሕሌት ተኽላይ መገደሏን፣ የክልሉ ማእከላዊ ዞን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የዞኑ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር ፀጋይ ኣስፈሃ ለአሜሪካ ድምፅ እንደተናገሩት፣ አጋቾቹ የ16 ዓመቷን አዳጊ ማሕሌት ተኽላይን ባገቱበት ዕለት ገድለው እንደቀበሯት፣ ፖሊስ ከተጠርጣሪዎች ማረጋገጡንና ቤተሰቦቿ የአዳጊዋን አስከሬን ዛሬ ረቡዕ መረከባቸውን ገልጸዋል፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓቷም፣ ዛሬ ከቀትር በኋላ መፈጸሙን ኮማንደሩ አክለው አስታውቀዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው የ“ይኾኖ” የሴቶች መብት ተሟጋች ሲቪል ማኅበረሰብ አስተባባሪ፣ መንግሥት፣ በተለይ ለሴቶች የደኅንነት ስጋት የኾነውን የክልሉን የጸጥታ ችግር ከኅብረተሰቡ ጋራ በመተባበር እንዲፈታ ጠይቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG