በዐማራ ክልል ካለው በትጥቅ የተደገፈ ግጭት ጋራ በተያያዘ፣ በእነአቶ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ የሽብር ክስ ከተመሠረተባቸው 52 ተከሳሾች መካከል፣ አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በእስር ላይ የሚገኙ 16ቱ ተከሳሾች፣ በዋስትና ጥያቄያቸውና በክስ መቃወሚያቸው ላይ የፍርድ ቤቱን ብይን ለመስማት፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ሰኔ 12 ቀን 2016 ዓ.ም. ችሎት ቀርበዋል፡፡
የተከሳሾቹ ጠበቆች እና ዐቃቤ ሕግ፣ ባለፈው ግንቦት 29 ቀን በነበረው ችሎት ላይ ያደረጉትን ክርክር ያደመጠው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የፀረ ሽብር እና ሕገ መንግሥታዊ ችሎት፣ ዛሬ ዋስትናውን ውድቅ ማድረጉን፣ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል፣ ከትላንት በስቲያ ሰኞ፣ የኢሕአፓን ሊቀ መንበር ጨምሮ ዋስትና የተፈቀደላቸው ዘጠኝ እስረኞች አልተፈቱም፡፡
አርቲስት ዐማኑኤል ሀብታሙንና የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳን ጨምሮ በ20 ግለሰቦች ላይም፣ ፖሊስ በድጋሚ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ይከታተሉ፡፡