በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመንግስታቱ ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት ወደ አዲስ አበባ ሊጓዙ ነው


The logo of the United Nations is seen on the outside of the U.N. headquarters in New York,
The logo of the United Nations is seen on the outside of the U.N. headquarters in New York,

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት ዴኒስ ፍራንሲስ ከዛሬ ቅዳሜ ሰኔ ስምንት እስከ ሰኔ 11/2016 ድረስ በአዲስ አበባ ቆይታ እንደሚያደርጉ የመንግስታቱ ቢሮ መግለጫ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንቱ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

በተመሳሳይ ፕሬዚዳንቱ አፍሪካ ህብረትንም እንደሚጎበኙ እና ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀመንበር ዶ/ር ሞኒክ ንሳንዛባጋናዋ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያደርጉም መግለጫው አክሎ አትቷል። በተጨማሪም ፕሬዚዳንቱ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሃፊ ቢሮ ሃላፊ ክሌቨር ጋቴት ጋት ኮሚሽኑ በቀጠናዊ የልማት ጥረቶች ላይ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ለማቅረብ ይገናኛሉ ብሏል።

ፕሬዚዳንቱ እና ሉዑካቸው ተጨማሪ ተወካዮችን እና የተለያዩ የመንግስታቱ ድርጅት እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር ውይይት እንደሚኖራቸው ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG