በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በጸጥታ ችግር ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሶብኛል አለ


ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በጸጥታ ችግር ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ ጉዳት ደርሶብኛል አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:04 0:00

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚገኘው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ፣ ባለፉት ሦስት ዓመታት፣ በመንግሥት የጸጥታ ኀይሎች እና በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት መካከል በቀጠለው ግጭት፣ ከአራት ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደርሶበታል፤ ሲሉ፣ የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የስኳር ፋብሪካው፣ በቀን እስከ ዐሥር ሺሕ ኩንታል የማምረት ዓቅም እንደነበረው ያወሱት ዋና ሥራ አስኪያጁ መንግሥቱ ኀይለ ማርያም፣ በግጭቱ የተነሣ በግማሽ መቀነሱን ገልጸዋል።

የፋብሪካው ሠራተኞች በበኩላቸው፣ በአካባቢው ፈታኝ የነበረው የጸጥታ ችግር አሁን መሻሻል ማሳየቱንና አንጻራዊ ሰላም መኖሩን አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG