ማላዊ ከሦስት ዓመታት የብዙሃን መገናኛ ነጻነትን የሚያፍኑ አንዳንድ ሕጎችን በመሰረዝ መሻሻል ያሳየች ቢሆንም በጋዚጠኞች ላይ የሚደርሰው ዛቻ እና እስር ተባብሶ መቀጠሉን የሀገሪቱ የሚዲያ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ተናገሩ። ማላዊ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በሚቀጥለው ዓመት ለምታካሂደው ጠቅላላ ምርጫ እየተዘጋጀች ባለችበት በዚህ ወቅት በፕሬስ ነጻነት ላይ የሚፈጸም ጥቃት እንደሚያሳስባቸው ብዙዎች ጋዜጠኞች ይገልጻሉ።
የቪኦኤው ጃማል ፕሪንስ ከሊሎንግዌ ያጠናቀረው ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።