በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታታሪዋ እናት ራህዋ - ከጎሚስታ እስከ ዘርፈ ብዙ ግብርና


ታታሪዋ እናት ራህዋ - ከጎሚስታ እስከ ዘርፈ ብዙ ግብርና
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:10 0:00

በአርባዕተ አስመራ ተወልደው ያደጉትና ዛሬ የስድስት ልጆች እናት ለኾኑት ወይዘሮ ራህዋ እዮብ፣ “ሥራ ጾታ የለውም” ይላሉ፡፡ በተለምዶ ለወንዶች ተብለው የሚተዉ የጉልበት ሥራዎችን ሳይቀር ለመከወን ብዙም እንደማይቸገሩ ወይዘሮዋ ይናገራሉ፡፡

ወይዘሮ ራህዋ፣ በፍራፍሬ ማምረትና በዓሣ ርባታ ላይ ተሰማርተው ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ። ሥራቸው በዐይነቱ እና በስፋቱ ብቻ ሳይኾን፣ በመገኛውም የተራራቀ ነው፡፡ የፍራፍሬ እርሻው በደቡብ ሪጅን በጾሮና፣ የንብ እርባታው በሰገነይቲ፣ የዓሣ እርባታው ደግሞ በአሥመራ ኣካባቢ ይገኛል፡፡

ከኹሉም በፊት ጎሚስታም እንደነበሩ ያወሱት ወይዘሮ ራህዋ፣ የሥራ ኃላፊነት እና ጫና ቢደራረብባቸውም፣ ዋናው ነገር “የመሥራት ፍላጎት እና ተነሣሽነት ነው፤” ይላሉ፡፡ ሕልማቸውን ለማሳካት የሚቸገሩ መስለው ባይታዩም፣ ከኅብረተሰቡ አንዳንድ አሳሪ ልማዶች አንጻር መሰናክልና ፈተና እንደሚገጥማቸው ግን አልሸሸጉም።

የአሥመራው ዘጋቢያችን ብርሃነ በርሀ፣ ጀንበር ካልጠለቀች የማያቆመውን የወይዘሮ ራህዋን የሥራ ውሎ ቃኝቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG