በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት የኪነ ጥበብ ሞያተኞችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ


ሦስት የኪነ ጥበብ ሞያተኞችን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:48 0:00

ከዐሥር እስከ ሰባ ቀናት ያህል ወደ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ታስረው የቆዩ ተጠርጣሪዎች፣ ትላንት ረቡዕ፣ ፍርድ ቤት ቀርበው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ተጠየቀባቸው።

ፖሊስ ፍርድ ቤት ያቀረባቸው፣ አርቲስት ዐማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ አመለ ወርቅ ፈይሳ እና በማኅበራዊ የትስስር ገጾች ላይ የምትታወቀውን ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 20 ተጠርጣሪዎችን ነው፡፡

እስረኞቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀል አድራጎቶችም፡- “በቡድን በመደራጀት ወጣቶችን መልምሎ በማሰማራት፣ ገንዘብ ለሽብር ቡድን ሎጂስቲክስ መግዣ በማዋልና መንግሥትን በኀይል ለመቀየር” የሚሉ መኾናቸውን ፖሊስ ለፍርድ ቤት አስታውቋል።

የተጠቀሱትን ጉዳዮች ለማጣራትም ፖሊስ ላቀረበው ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጥያቄ፣ ፍርድ ቤቱ 13 ቀናትን ፈቅዶለታል።

XS
SM
MD
LG