ኤልሳቤጥ ድንቁ፣ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት፣ በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወንጪ ወረዳ በጨቦ የገጠር መንደር ውስጥ፣ በአካባቢው የመጀመሪያውን ቤተ መጻሕፍት ከፍታለች።
ኤልሳቤጥ፣ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የክልል ከተሞች፣ ሕፃናት ትምህርት አቋርጠው ለጉልበት ብዝበዛ መዳረጋቸውና ከትምህርት መራቃቸው እንደሚያሳስባት ትገልጻለች።
“ይሥሓቅ ድንቁ መታሰቢያ”፥ ኤልሳቤጥ በሕይወት በሌለው ታላቅ ወንድሟ ስም የከፈተችው ቤተ መጻሕፍት እና የሕፃናት መጫወቻ ነው፡፡ የማንበብ እና የመጻፍ ፍቅር በአሳደረባት ታላቅ ወንድሟ ስም የከፈተችውን ይህን ቤተ መጻሕፍት፣ በሳምንት ከኀምሳ በላይ ሕፃናት እንደሚጎበኙት ተገልጿል።
ማኅበረሰብ ተኮር የኾነው መጻሕፍት ቤት፣ በአካባቢው ሕፃናት የማንበብ ክህሎት ላይ ትልቅ ለውጥ ማስመዝገቡን፣ የአካባቢው አርሶ አደሮች ይመሰክራሉ።
ጋዜጠኛ እና መምህርት ኤልሳቤጥ ድንቁ፣ አንድ የልጆች መጽሐፍም ለኅትመት አብቅታለች።
ኤልሳቤጥንና አርሶ አደር ሰሎሞን ደስታን አነጋግራ ኤደን ገረመው ያሰናዳችውን ዘገባ ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም