በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር እና የባለሞያዎች አስተያየት


የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ንግግር እና የባለሞያዎች አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:34 0:00

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ፣ በዓድዋ ሙዚየም መሰብሰቢያ አዳራሽ የተካሔደውን የአገራዊ ምክክር ባለድርሻ አካላት ውይይት በንግግር ሲከፍቱ፣ “ከእንግዲህ በኢትዮጵያ የሽግግር መንግሥት አይኖርም፤" በማለት ያንጸባረቁት አቋም፣ የኮሚሽኑን ገለልተኝነትና የምክክሩን ተቀባይነት የሚጎዳ ነው፤ በሚል ትችት እየቀረበበት ነው።

በሌላ በኩል፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ሐሳቡ ለውይይት እንዳይቀርብ አድርገው አልተናገሩም፤ በሚል የሚሞግቱም አሉ።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ በበኩሉ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አስተያየት፣ እንደ አንድ የመንግሥት ሐሳብ ብቻ ኾኖ እንደሚመዘገብ ጠቅሶ ምላሽ ሰጥቷል።

XS
SM
MD
LG