በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኬኒያ እንደራሴዎች በብሪታኒያ የጦር አሠልጣኞች ተፈጽሟል የተባለን ወንጀል እየመረመሩ ናቸው


የኬኒያ እንደራሴዎች በብሪታኒያ የጦር አሠልጣኞች ተፈጽሟል የተባለን ወንጀል እየመረመሩ ናቸው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:58 0:00

ኬኒያ ውስጥ ሥልጠና በሚያካሒዱ የብሪታኒያ የጦር ሰዎች “ተፈጽሟል” የተባለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት፣ በኬኒያ ምክር ቤታዊ ኮሚቴ እየተመረመረ መኾኑ ተገለጸ፡፡

ምክር ቤታዊው ኮሚቴው፣ ከዐሥር ዓመታት በፊት ተጀምሮ እስከ አሁን ምርመራው ያልተቋጨውን የአንዲት ሴትን ኅልፈት ጨምሮ፣ የመብቶች ጥሰቶች ፈጽመዋል ስለተባሉት ወታደሮች ከነዋሪዎች ለመስማት ወደ ማዕከላዊ ኬኒያ ተጉዟል፡፡

ምክር ቤቱ፣ ኮሚቴውን አቋቁሞ የማጣራት ሥራውን የጀመረው፣ ተፈጽመዋል በተባሉት የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች፣ የብሪታኒያን የጦር ሠራዊት ተጠያቂ እንዲያደርግ፣ የኬኒያ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባቀረበው ጥያቄ መሠረት እንደኾነ ታውቋል፡፡ መሐመድ ዩሱፍ ከናይሮቢ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጂት ታየ ታቀርበዋለች፡፡

XS
SM
MD
LG