በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

'ሃማስ ስምምነቱን ከተቀበለ እስራኤልም ትቀበላለች' አሜሪካ


ፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ታል-ሱልጣን ራፋህ በሚገኝ አንድ መንደር በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ሌሊቱን በተመታ ፍርስራሽ ላይ ተቀምጠዋል
ፍልስጤማውያን በደቡባዊ ጋዛ ታል-ሱልጣን ራፋህ በሚገኝ አንድ መንደር በእስራኤል የቦምብ ጥቃት ሌሊቱን በተመታ ፍርስራሽ ላይ ተቀምጠዋል

የዋይት ኋውስ የብሄራዊ ደህንነት ቃል አቀባይ ጆን ከርቢ፣ ሃማስ በታቀደው የእርቅ ስምምነት ከተስማማ ዩናይትድ ስቴትስ እስራኤል እቅዱን እንደምትቀበል ትጠብቃለች ብለዋል፡፡

ጋዜጠኞች እና የፍልስጤም የጤና ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ እንደተናገሩት እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት በትንሹ 11 ሰዎች ተገድለዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ጦርነቱን ማቆም እና በሃማስ የተያዙ አንዳንድ ታጋቾችን መልቀቅን ያካተተ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ግፊት እያደረገች ነው።

የእስራኤል ጦር በጋዛ ከ50 በላይ ዒላማዎች ላይ የአየር ድብደባ እንዳደረገ እና በማዕከላዊ ጋዛ እና ራፋህ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ እግረኛ ወታደሮች እንዳሉት ገልጿል።

የእስራኤል መከላከያ ሠራዊት ባለፈው ጥቅምት በሃማስ ጥቃት ታፍኖ ሳይወሰድ አልቀረም ያለው ዶሌቭ ዮሁድን መገደሉንና አስክሬኑን እንዳገኘ አስታውቋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የሰላም ዕቅዱን ከእስራኤል ባለሥልጣናት ጋር ትላንት እሁድ ተነጋግረውበታል፡፡ ዕቅዱ “የእስራኤልን የረጅም ጊዜ ደህንነት ያስጠብቃል” ብለዋል፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት እስራኤል ጋዛን የሚመራውን ሃማስ እንደማትቀበል ገልጸው ከእስላማዊው ቡድን ውጭ ሌሎች አማራጮችን እየፈለገች ነው ብለዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ እስራኤል ጦርነቱን ለማስቆም ካስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች መካከል የሃማስን አቅም ማውደም፣ ታጋቾችን ማስፈታት እና ጋዛ ለእስራኤል ስጋት እንዳትሆን ማረጋገጥ የሚሉት ይገኙበታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ባላፈው ዓርብ የሰላም ስምምነቱ የእስራኤልን ወታደሮች በከፊል ለቆ መውጣት፣ አንዳንድ ታጋቾችን መልቀቅን ጨምሮ ለስድስት ሳምንታት የሚቆይ የተኩስ አቁምን እንደሚያካትትና በአስታራቂዎች አማካይነት “ጠላትነትን ለዘለቄታው የማብቃት” ድርድር እንደሚደረግ ተናግረዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG