በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትራምፕ የተላለፈባቸው የጥፋተኝነት ብይንና የሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች ዘመቻ


ትራምፕ የተላለፈባቸው የጥፋተኝነት ብይንና የሁለቱ ፕሬዚዳንታዊ ዕጩዎች ዘመቻ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:39 0:00

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በገንዘብ ነክ ሰነዶች ላይ ፈጽመውታል በተባለው የማጭበርበር ድርጊት፣ ከሕዝብ የተውጣጡ ዳኞች የጥፋተኝነት ብይን ሰጥተዋል፡፡ ይህንም ተከትሎ፣ በሚቀጥለው ወር የእስር ቅጣት ሊፈረድባቸው መኾኑ ተመልክቷል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ፍርደኛው ትራምፕ፣ ትላንት እሑድ የበኩላቸውን አስተያየት ሰንዝረዋል። ከዚህ ሁሉ በፊት ግን፣ የትራምፕም የባይደንም የምረጡኝ ዘመቻዎች፣ የጥፋተኝነቱን ውሳኔ ደጋፊዎቻቸውን ለማነቃቃት መጠቀም ይዘዋል።

እንደተንታኞች አስተያየት ግን፣ የትኛውንም ወገን ለመደገፍ ገና ያልወሰኑ መራጮችን መሳብ ያን ያህል ቀላል አይኾንም።

ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሌሲያስ ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG