በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኔታኒያሁ የባይደንን ጋዛ ዕቅድ ‘መልካም ውል ባይሆንም’ እስራኤል ትቀበለዋለች አሉ


በቴል አቪቭ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁን ለመቃወም የወጡ ሰልፈኞች
በቴል አቪቭ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታኒያሁን ለመቃወም የወጡ ሰልፈኞች

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ረዳት ዛሬ እሁድ በጋዛ የሚገኘውን ጦርነት ለማቆም በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የቀረበውን ማዕቀፋዊ ስምምነት መቀበላቸውን አረጋግጠዋል። ይሁን እንጂ ኔታኒያሁን እቅዱ ችግር ያለበት እና ተጨማሪ ስራ የሚሻ ነው ሲሉም ነው የገለጹት።

"መታየት ያለባቸው ብዙ ዝርዝር ጉዳዮች አሉ" ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ “የእስራኤል ሁኔታ፣ የታጋቾቹን መፈታት እና ሀማስ ዘር አጥፊ አሸባሪ ድርጅት መሆኑን በተመለከተ ግን ምንም ለውጥ የለም” ብለዋል።

ባይደን ላለፉት ወራት አርብ ዕለት ካቀረቡት የስምምነት ማዕቀፎች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው በርካታ የተኩስ አቁም ሀሳቦችን ቢያቀርቡም ይሁን እንጂ እስካሁን ድረስ ሁሉም ተቀባይነት ሳያገኙ ቀርተዋል። ባይደን በጎርጎሮሳዊያኑ የካቲት ወር እስራኤል በረመዳን ቅዱስ የጾም ወቅት ጦርነት ለማስቆም ተስማምታለች ቢሉም እርቁ ተፈጻሚ ሳይሆን ቀርቷል።

እስካሁን ድረስም በዋናነት እስራኤል ሀማስ እስኪወድም ድረስ ጦርነቱን ለጊዜው ብቻ በማቆም እንደምትወያይ አሳይታለች። ባይደን በቅርቡ ባደርጉት ንግግር “ሀማስ ስልጣን ከሌለው በጋዛ የተሻለ ቀን ይፈጠራል” ያሉ ሲሆን ይሁን እንጂ ይህ እንዴት እንደሚሳካ የሰጡት ማብራሪያ የለም።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG